ለዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥ የበለጠ መረጃ ማግኛ መንገዶች ስልክ ቁጥር፡- 011 666 33 74 ወይም ነፃ የጥሪ መስመር ስልክ ቁጥር 9417 ይጠቀሙ!

አዲስ አበባ የፌደራል መንግስት መቀመጫ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ዋና ከተማ እና መቀመጫ፣ የብዙ አለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ እና መኖሪያ እንዲሁም የተለያዩ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ተዋዶ እና ተቻችሎ የሚኖሩባት ከተማ እንደመሆኗ እጅግ በጣም ብዙ ተሸከርካሪዎች እና  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝብ  በየዕለቱ በከተማ ውስጥ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚንቀሳቀሱ ተሸከርካሪዎች መግብያ እና መውጫ ኮሪደር ሆና እያገለገለች ትገኛለች፡፡ ይህንን ግዙፍ የተሸከርካሪ ፍሰትን ለማሳለጥ እንዲሁም የህብረተሰቡን የትራንስፖርት ችግርን ለመቅረፍ የአዲስ አበባ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ላለፉት ዓመታት ከመንገድ መስራት ልማት ማስፋፋት ጀምሮ የትራፊክ ፍሰትን ከማሻሻል አንፃር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ሲያከናወን ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ በከተማ ውስጥ የነዋሪዎች ቁጥር በእጅጉ በመጨመሩ የአቅርቦት እና ፍላጎት ሊመጣጠን አልቻለም፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ቢሮው ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን በ2011 በጀት ዓመት የመንገድ መስረተ ልማት መስፋፋት እና ነባሩንም መጠገን፣ የትራፊክ ፍሰትን ሊያሳልጡ የሚችሉ ስራዎችን ለማከናወን፣ የብዙሃን ትራንስፖርት ቁጥር እና አገልግሎት ለመጨመር፣ በትራንስፖርት ዘርፈ ችግር ፈቺ ጥናቶች ለማከናወን፣ አሽከርካሪዎች የሞያ ብቃት አገልግሎት እና የተሸከርካሪዎች የቴክኒክ ችግር ለመቅረፍ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ይህንን ግዙፍ ስራ ለማከናወን ሙሉ ኃላፊነት የተጣላባቸው ተጠሪ ተቋማቶች የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ አሁን የመጣውን ለውጥ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የላቀ ውጤት የምታስመዘግቡበት አመት እንዲሆንላችሁ እየተመኘው የከተማችን ነዋሪዎችም የአዲስ አበባ መንገድና ትንስፖርት ቢሮ በምናከናውናቸው ስራዎች ከጎናችን ቆማችሁ አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ እንድታደርጉ ከአደራ ጭምር አቀርባለሁ፡፡ መልካም የስራ ዘመን ይሁንልን ፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ !!!!

 

ይህንን እንደመነሻ ሃሳብ ይወሰድና በተለይ በቀጣይ ወራት እና ዓመቱን ሙሉ ትኩረት ልንሰጥባቸው የሚገቡትን ጉዳዮች እንደመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ በዘርፉ ያሉትን አገልግሎቶች በተመለከተ አጉልተው በአንክሮ እንድንመለከታቸው የጽ/ቤቱ መልዕክትዎን ያስቀምጡልን!

እናመሰግናለን!





የቢሮው ስትራቴጂያዊ ግቦች

  1. ስትራቴጂያዊ የከተማ ትራንስፖርት ስራ አመራር

  2. የትራንስፖርት መሠረተ ልማት

  3. የትራንስፖርት አገልግሎት

  4. የዘርፉን አቅም ማጎልበት





የቢሮው ራዕይ

“በ2022 አዲስ አበባ  ተደራሽ ፣ አስተማማኝ ፣ምቹ ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ውጤታማ እና ከባቢያዊ ተስማሚነቱ የተረጋገጠ የትራንስፖርት ስርዓት ያላት ከተማ ሆና ማየት”

 

የቢሮው ተልዕኮ

በከተማዋ የሚታየውን የትራንስፖርት መሠረተ-ልማትና አገልግሎት አቅርቦት ችግሮችን በጥናት በመለየትና  ተግባራዊ እንዲሆን በማድረግ ፣ የትራንሰፖርት ዘርፉን ዘላቂ የልማት ስትራቴጂዎችን በማዘጋጀትና ተግባራዊ በማድረግ፣ የተለያዩ የህዝብና የጭነት ትራንስፖርት ስርዓትን ለማሻሻል የሚረዱ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ፣  የመንገድ ደህንነትን ለመሻሻል የሚረዱ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ፣ የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል እና የትራንስፖርት ዘርፉን አቅም በማሳደግ አስተማማኝ፣ተደራሽ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ወጪ ቆጣቢና አካባቢያዊ ተስማሚነቱ የተረጋገጠ የከተማ ትራንስፖርት ስርዓትን መዘርጋት፡፡ 

እንደተቋም የተለዩ አንኳር ባህሎቻችን/ተቋማዊ ባህሎቻችን/

  • ተግባብቶ መስራት፣

  • ሙያዊ ስነ-ምግባርን ጠብቆ መስራት፣

  • ችግር ፈቺ መሆን፣

  • የተቋሙን መልካም ገፅታ መገንባት፣

  • ውጤታማ ስራ መስራት